የእግዚአብሔር ልጅ: (Amharic edition) (Afrikaans Edition) - Softcover

  • 4.73 out of 5 stars
    11 ratings by Goodreads
9789994430543: የእግዚአብሔር ልጅ: (Amharic edition) (Afrikaans Edition)

This specific ISBN edition is currently not available.

Synopsis

ይህንን “የእግዚአብሔር ልጅ” የተሰኘ ድንቅ መጽሐፍ ከጥግ እስከ ጥግ ያነበብኩት በብዙ ፍላጎትና በተማሪ ልብ ነው። ነገረ ክርስቶስን የመሰለ ከባድ አስተምህሮ በሚያስገርም ጥልቀት፤ ግን ብዙኀን ሊረዱት በሚችሉት ግልጥነትና ፍሰት መጻፍ አስደናቂ ሊቅነት ነው። ወንድማችን ጳውሎስ ፈቃዱ እንዲህ ዐይነት ተሰጥኦ በጸጋ የተቸረው ሰው ነው። መጽሐፉ በዋንኛነት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ላይ ያተኰረ ቢሆንም፣ የትምህርተ ሥላሴን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ይተነትናል። ወቅታዊ አከራካሪ ጕዳዮችንም በማንሣት ግልጽ ምላሾችን ይሰጣል። በእኔ አመለካከት ይህ መጽሐፍ የእምነታችን ማዕከል የሆነውን ክርስቶስን በተሻለ ጥልቀት እንድንረዳ የሚያግዝ ስንቅ፣ እምነታችንንም ከስሕተት እንድንመክት የሚረዳ ትጥቅ ነው። ሁላችን መጽሐፉ በየግላችን እንዲኖረን፣ እንድናነብና እንድንታነጽበት አበረታታለሁ። ማሙሻ ፈንታ (ዶ/ር)ይህ መጽሐፍ፣ አምላክነትና ሰውነት በአንዱ ክርስቶስ እንዴት ተኳኳኑ? በሚለው ጒዳይ ላይ ጥልቅ ትንተናዎችን ይዟል። ጸሐፊው የነገሩን ምስጢርነት በመገንዘቡ ምስጢር የሆነውን ነገር ለመበተን ሙከራ አላደረገም። መግለጥ እስከሚቻልበት ደረጃ ግን ተጒዟል። ነገሩን ለማስረዳትም ከዘመንተኞቹ ሊቃውንት ጀምሮ እስከ ጥንቶቹ አባቶች ድረስ ብዙ ዋቢዎችን ጠቅሷል። በክርስቶሳውያን ዘንድ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ይታወቃል። ይሁንና የክርስቶስ ልጅነት መቼ ጀመረ? ወይስ ልጅነቱ ዘላለማዊ ነው? ልጅነቱ ዘላለማዊ ከሆነ ከድንግል ማርያም ስለ መወለዱና ሥጋ ስለ መሆኑ የተሰጡትን ገለጻዎች እንዴት እንረዳቸው? እነዚህና ሌሎችም ጥያቄዎች ተገቢ መልስ አግኝተዋል። በእኔ እምነት ይህ መጽሐፍ ዝርዝር ነገረ ክርስቶሳዊ ትንተናዎችን በመስጠት ረገድ የመጀመሪያው ፈር ቀዳጅ መጽሐፍ ነው። ምኒልክ አስፋውወንድማችን ጳውሎስ ፈቃዱ “ነገረ ክርስቶስ የነገረ መለኮት መነሻ ብቻ አይደለም፤ ማዕከላዊ ነጥቡም ነው” ሲል አበክሮ ይነግረናል። የቤተ ክርስቲያን ሥረ መሠረቷ የተዋቀረው፣ እምነታችንም ይሁን ኑሮአችን የተቃኘው፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን ማወቃችን የተማከለው በዚሁ ላይ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ከአባቱ ዘንድ ተልኮ የመጣ ልጅ ነው። ግና “መቼ ነው ልጅ የሆነው?” ከውልደቱ አስቀድሞ? ወይስ በኋላ? በትንሣኤው? ከእርሱ የተነሣ ልጆች ሆንን ሲባልስ ምን ማለት ነው? እነዚህንና ሌሎች መሠረታዊ ጥያቄዎችን መጽሐፉ ይዳስሳል። በዚህ መጽሐፍ ጳውሎስ ጠንቃቃ፣ ልከኛ፣ የቃላት አጠቃቀሙ ግልጽ፣ አቀራረቡ ትህትናን የተላበሰና ጤናማ የነገረ መለኮት አወቃቀርን የሚከተል ነው። የነገረ ክርስቶስን ምጋቤያዊና ተግባራዊ ፋይዳውንም አይዘነጋም። በአጭሩ፣ ክርስቶስን አብ በመንፈሱ አማካኝነት እንደገለጠው መልሶ ለመግለጥ ጥንቃቄ ያደርጋል። እጅግ ጠቃሚና ድንቅ መጽሐፍ ነው።ሳምሶን ጥላሁንይህ መጽሐፍ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” ሲሉ ምን ማለታቸው እንደ ሆነ የሚያትት ነው። መጽሐፉ በቀደምት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በነገረ ክርስቶስ ላይ የተነሡ ጥያቄዎችን ለመመለስ አልተጻፈም። ይልቁንም፣ በየምስባኮቻችን የተለመዱትን በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ላይ ያሉ የተዛቡ አመለካከቶች ለመሞገትና ለማረቅ የተጻፈ ነው። የአሁኒቷ ቤተ ክርስቲያን የቤት ሥራዎች እነዚህ ናቸው። ጳውሎስ ሙያዊ የነገረ መለኮት ቃላትን አለመጠቀሙ፣ አንባቢ ሳይሰላች ጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳቶችን እንዲገነዘብ ያደርጋል። መጽሐፉን አንብቤ ስጨርስ፣ “ለካ! ጥልቅ የሆነ የምርምር መጽሐፍ ሣር ሣር እንዳይል ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል” እንድል ሆኛለሁ፤ ስለዚህ ስጦታው እግዚአብሔርን አመስግኛለሁ። ዮሐንስ መሐመድ (መጋቢ)

"synopsis" may belong to another edition of this title.

(No Available Copies)

Search Books:



Create a Want

Can't find the book you're looking for? We'll keep searching for you. If one of our booksellers adds it to AbeBooks, we'll let you know!

Create a Want